በክልል ወጣቶችን በስንዴ ልማት በስፋት ለማሰማራት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

90

ሀዋሳ መስከረም 26/2015 (ኢዜአ) በደቡብ ክልል በኢንተርፕራይዝ የተደራጁ ወጣቶችን በስንዴ ልማት ለማሰማራት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ የሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ አስታወቀ።

በቢሮው በክልሉ የተለያዩ ዞኖች ውስጥ በኢንተርፕራይዞች የለማ የመኸር ሰብል አስጎብኝቷል ።

ጉብኝቱም ጉራጌ፣ ሲልጤ እና ሀላባ ዞኖች በኢንቸርፕራይዞች እየለማ ያለ የመኸር እርሻ እንቅስቃሴ ያከተተ ነው።

በተጨማሪም በክልሉ በሀዳያ ዞን ሻሾጎ ወረዳ ውስጥ በስንዴ፣ ቦቆሎና ጤፍ የለማ ማሳ ተጎብኝቷል።

በወቅቱ የቢሮው ኃላፊ አቶ ቢረጋ ብርሀኑ እንደ ሀገር በስንዴ ምርት ራስን ከመቻል ባለፈ ወደ ውጭ ለመላክ የተያዘውን ግብ ለማሳካት እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

እየተሰራ ያለው ልማትም እንደ ሀገር  የተያዘውን ራዕይ ለማሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚኖረው መሆኑን በማከል።

በ2014/15 መኸር እርሻ 13 ሺህ የሚጠጉ የተደራጁ ወጣቶች በሰብል ልማት ማሳተፍ መቻሉንም ተናግረዋል።

በመስክ ምልከታው ላይ ከክልሉ ሁሉም ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች የተውጣጡ የዘርፉ አመራሮች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም