የትግራይ ክልል ተወላጆች አሸባሪውን ህወሃት የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ ከአሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት አካሄዱ

263

መስከረም 24 /2015 (ኢዜአ) በአዲስ አበባ የሚኖሩ የትግራይ ክልል ተወላጆች አሸባሪውን ህወሃት የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ ከአሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት አካሄዱ።

ሰልፈኞቹ ባነገቡትና ባሰሙት መፈክር እንደገለጹት አሸባሪው ህወሃት ከህዝብ ፍላጎት በተቃራኒ ለሽብር ዓላማ የቆመ መሆኑን አስገንዝበዋል።

May be an image of 9 people, people standing, tree and outdoors

አሸባሪው ህወሃት ለ3ተኛ ጊዜ የከፈተውን ጦርነት እንዲያቆም አለም አቀፉ ማህበረሰብ ጫና እንዲያደርግበት ጠይቀዋል።

ህወሃት የትግራይ ህጻናትንና ሴቶችን በጦርነት መማገዱን ሊያቆም ይገባል ብለዋል።

May be an image of 12 people, people standing and road

አሜሪካና ሌሎች ምእራባዊያን የሽብር ቡድኑ ከድርጊቱ እንዲቆጠብ ሊያሳስቡ እንደሚገባም ገልጸዋል።

ሰልፈኞቹ በቀጣይም በእንግሊዝና በእስራኤል ኤምባሲዎች በር ላይ ድምጻቸውን ያሰማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም