ኢንዱስትሪ ሚኒስቴርና በስሩ ያሉ ተጠሪ ተቋማት ለመከላከያ ሠራዊት 16 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረጉ

130

መስከረም 23/2015 (ኢዜአ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴርና በስሩ ያሉ ተጠሪ ተቋማት ለጀግናው የአገር መከላከያ ሰራዊት 16 ሚሊዮን ብር የገንዘብና የአይነት ድጋፍ አደረጉ፡፡

ድጋፉን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ለመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሊዊጂ አስረክበዋል፡፡

የሚኒስቴሩና ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች ለሠራዊቱ ያላቸውን አጋርነት ለማሳየት ድጋፉን ማበርከታቸውን ነው ሚኒስትሩ የተናገሩት።

በቀጣይም የሚደረገው ሁለንተናዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሊዊጂ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሠራዊቱን በመደገፍ እያደረገው ያለውን ርብርብ በተሰማራበት መስኮች በመድገም ለአገር ሠላም መከበር የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ አመላክተዋል።

ሚኒስቴር መስሪያቤቱና ተጠሪ ተቋማት ላደረጉት ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም