ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ

354

መስከረም 23 /2015 (ኢዜአ) የ2015 ዓ.ም ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የአንደኛ ሳምንት መርሐግብር የመጨረሻ ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ።

ከቀኑ 7 ሰአት ፋሲል ከነማ ከአዳማ ከተማ እንዲሁም መቻል(በቀድሞ ስያሜው መከላከያ) ከሀዲያ ሆሳዕና ከቀኑ 10 ሰአት በባህር ዳር ስታዲየም ይጫወታሉ።

ትናንት በተደረጉ ጨዋታዎች ለመጀመሪያ ጊዜ በፕሪሚየር ሊጉ የተሳተፈው ለገጣፎ ለገዳዲ ሐዋሳ ከተማን በካርሎስ ዳምጠው ሁለት ግቦች 2 ለ 1 አሸንፏል።

ዓሊ ሱሌይማን ለሐዋሳ ከተማ ብቸኛውን ግብ አስቆጥሯል።

ድቻ ስፖርት ክለብ ከኢትዮጵያ ቡና ያደረጉት ጨዋታ ያለ ምንም ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት መርሐግብሮች ከነገበስቲያ መካሄድ ይጀምራሉ።

የዘንድሮው ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር መርሐ ግብሮች በባህር ዳር ስታዲየም(ከአንደኛ እስከ አምስተኛ ሳምንት)፣በድሬዳዋ ስታዲየም (ከስድስተኛ እስከ 10ኛ ሳምንት) እንዲሁም በአዳማ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ ሜዳ(ከ11ኛ እስከ 15ኛ ሳምንት) ይከናወናሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም