የኢሬቻን ዘርፈ ብዙ እሴቶች ጠብቆ በማስቀጠል በአንድነት ለጋራ እድገት መስራት አለብን -- የበዓሉ ተሳታፊዎች

112

መስከረም 22/2015 (ኢዜአ) የኢሬቻን ዘርፈ ብዙና ጥልቅ እሴቶች ጠብቆ በማስቀጠል በአንድነት ለጋራ እድገት ሁላችንም መስራት አለብን ሲሉ የሆራ-ሀርሰዴ በዓል ተሳታፊዎች ተናገሩ።

የ2015 ዓ.ም የኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ እና በቢሾፍቱ ከተሞች በተካታታይ ቀናት በድምቀት ተከብሯል።

በዓሉ ባህላዊ ስርዓቱን ጠብቆ በልዩ ድምቀት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ታዳሚዎች በተሳተፉበት ተከብሯል።

በቢሺፍቱ ሆራ-ሀርሰዲ ኢዜአ ያነጋገራቸው የበዓሉ ታዳሚዎች የኢሬቻ በዓል የፍቅር፣ ወንድማማችነትና አብሮነት መገለጫዎች ለኢትዮጵያዊ አብሮነት ጥሩ መሰረት የሚያስይዙ መሆኑን ገልጸዋል።

የበዓሉ ታዳሚ አባገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎችና ፎሌዎችም ኢሬቻ የሚጠይቀውን ባህላዊ ስርዓት በመላበስ ለኢትዮጵያ ሰላም፣ አንድነትና ልማት የሚያመሰግኑበት በዓል ሆኖ ማለፉን ተናግረዋል።

በዓሉ የመላ ኢትዮጵዊያን ሃብትና የዓለም ቅርስ ጭምር በመሆኑ እሴቶቹን ጠብቆ በማስቀጠል በአገራዊ አንድነት ለጋራ እድገት መስራት አለብን ነው ያሉት።

የበዓሉን አጋጣሚም የአንድነትና የመተሳሰብና የመገናኛ መድረክ አድርገው እንደሚጠቀሙበት በመጠቆም።

የበዓሉ ስርዓትም ከገዳ ስርዓት የሚቀዳ የሰላም፣ የአንድነትና የመተሳሰብ ተምሳሌት መሆኑን ተሳታፊዎቹ ጠቅሰዋል።

የኢሬቻን የፍቅር፣ የመተሳሰብና የአንድነት እሴቶች ጠብቆ በማስቀጠል በአገራዊ አንድነት ለጋራ እድገት ሁላችንም መስራት አለብን ሲሉ ነው የተናገሩት።

በአዲስ አበባና በቢሾፍቱ በተከታታይ ቀናት የተከበረው የ2015 ዓ.ም የኢሬቻ በዓል ሰላማዊ ሆኖ መከበሩን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም