በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በሚካሄደው የሴካፋ ከ17 ዓመት በታች የእግር ኳስ ውድድር ላይ 6 ሀገራት ይሳተፋሉ

265

መስከረም 22 /2015 (ኢዜአ) በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በሚካሄደው የሴካፋ ከ17 ዓመት በታች የእግር ኳስ ውድድር ላይ ስድስት ሀገራት ይሳተፋሉ።

የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ሀገራት የእግር ኳስ ማህበራት ምክር ቤት(ሴካፋ) ከ17 ዓመት በታች የእግር ኳስ ውድድር ከመስከረም 21 እስከ ጥቅምት 9 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚካሄድ ቀን ተቆርጦለት ነበር።

ይሁን እንጂ ይሳተፋሉ ተብሎ የሚጠበቁ 4 ብሔራዊ ቡድኖች በተለያየ ምክንያት ባለመሳተፋቸው ቀድሞ የወጣው የምድብ ድልድል ዛሬ በድጋሚ እጣ ወጥቶ ከነገ ጀመሮ በስድስት አገራት መካከል ጫወታው እንደሚደረግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ገልጿል።

ነገ በሚጀመረው ውድድር ላይ ኢትዮጵያ፣ደቡብ ሱዳን፣ብሩንዲ ሶማሊያ፣ዩጋንዳና ታንዛኒያ የሚሳተፉ ሀገራት ናቸው።

የሴካፋ ከ17 ዓመት በታች የእግር ኳስ ውድድር ከመስከረም 23 እስከ ጥቅምት 5 ቀን 2015 ዓ.ም በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም