“የሆራ-ሀርሰዴ” ኢሬቻ ባህላዊ ሥርዓቱን ጠብቆ በመከበር ላይ ነው - ኢዜአ አማርኛ
“የሆራ-ሀርሰዴ” ኢሬቻ ባህላዊ ሥርዓቱን ጠብቆ በመከበር ላይ ነው
289
መስከረም 22/2015 (ኢዜአ) በቢሾፍቱ ከተማ እየተከበረ የሚገኘው “የሆራ-ሀርሰዴ” ኢሬቻ በዓል ባህላዊ ሥርዓቱን ጠብቆ በመከበር ላይ ነው።
የበዓል ተሳታፊዎች በዓሉ ወደሚከበርበት ስፋራ በመሄድ የያዙትን ለምለም ሳር በሆራ-ሀርሰዲ ሀይቅ በመንከር ባህላዊ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ የክረምቱን ጨለማ ዘመን አሳልፎ ወደ ብርሀን ላሸጋገረ ፈጣሪ ምስጋና እያቀረቡ ይገኛሉ።
በዓሉ በአንድነት፣ በመከባበርና በፍቅር በሀይቁ ዳርቻ ከጥዋቱ 11 ሰዓት ጀምሮ በድምቀት እየተከበረ ነው።
ከኦሮሚያ ክልል እና ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በዓሉን ለመታደም የመጡ እንግዶች በዓሉ ወደሚከበርበት “የሆራ-ሀርሰዴ ሀይቅ” ሲያቀኑ በባህላዊ አልባሳት ተውበው ህብረ ዜማና ጭፈራ ታጅበው እየተጓዙ ይገኛል።