ሐረማያ ዩኒቨርስቲ በህክምና ሙያ ያሰለጠናቸው ከ500 በላይ ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው

272

ሐረር ፤ መስከረም 21/2015(ኢዜአ) ፡- የሐረማያ ዩኒቨርስቲ ጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ በተለያየ የህክምና ሙያ ያሰለጠናቸው 502 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው።

ኮሌጁ በ25 ኛው ዙር እያስመረቃቸው ካሉት መካከል  115  በህክምና ዶክትሬት፤  ቀሪዎቹ ደግሞ በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም የሰለጠኑ መሆናቸው ተገልጿል።

ከሰለጠኑባቸው መስኮችም ጤና መኮንን፣ ፋርማሲ ፣አካባቢ ጤና አጠባበቅ ሳይንስ፣ አዋላጅና ክሊኒካል ነርስ  የሚገኙበት ሲሆን፤ ከጠቅላለው ተመራቂዎች  194  ሴቶች መሆናቸው ተመልክቷል።

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ  የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪና ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ   ሚስራ አብደላ፣የዩኒቨርሲቲው የስራ አመራር ቦርድ አባላት፣ የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮችና መምህራን እንዲሁም የተመራቂ ቤተሰቦች መታደማቸውን የኢዜአ ሪፖርተር ከሥፍራው ዘግቧል።