የባህላዊና ዘመናዊ ሙዚቃ አቀንቃኙ አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

554

መስከረም 17 / 2015 (ኢዜአ) የባህላዊና ዘመናዊ ሙዚቃ አቀንቃኙ አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።አርቲስቱ ባደረበት ሕምም ምክንያት በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ሕይወቱ ማለፉን ኢዜአ ከቅርብ ወዳጆቹ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

በጎንደር የተወለደው ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ለሙዚቃ ካለው ፍቅር የተነሳ በተወለደበት አቅራቢያ የሚገኝ የወታደር ካምፕ በመግባት በካምፑ በሚገኝ ኦርኬስትራ ውስጥ መዝፈን ጀመረ።

በድምጹ የተገረሙት ወታደሮች “ማዲንጎ” የሚል ስያሜ ያወጡለት ሲሆን ሕይወቱ እስካለፈበት ጊዜ በዚሁ ስም ሲጠራ ቆይቷል።

በ10 ዓመቱ ወደ አዲስ አበባ “ዜማ ላስታስ” ባንድ በመግባት የሙዚቃ ሕይወቱን ቀጥሏል።

ድምጻዊ ማዲንጎ “ስያሜ አጣሁላት”፣ “አማን ነው ወይ ጎራው” እና “ትዝታ” በሚባሉት ዘፈኖቹ ይታወቃል።

ድምጻዊ ማዲጎ አፈወርቅ ሙዚቀኛ ዘመን የሚሻገር ስራዎችን የሰራ ነው።

ኢትዮጵያ በተፈተነችበት ወቅት እያመመው ግንባር ድረስ በመሄድና ማሰልጠኛም ምልምሎችን በማነቃቃት የራሱ የሆነ ታሪክ የሰራ አርቲስት ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም