ኢትዮጵያውያኑ በጀርመን በተካሄደ የስዕል ውድድር አሸነፉ

87

መስከረም 16 /2015(ኢዜአ) ኢትዮጵያውያኑ የስነ ጥበብ ትምህርት ተማሪዎች በጀርመን ሌፕዥግ ከተማ በተካሄደ የስዕል ውድድር ማሸነፋቸው ተገለጸ።

በእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የስነ ጥበብ ትምህርት ክፍል ሠልጣኝ የሆኑት ፍሬወይኒ እንድሪያስ እና ኢዮብ እሸቱ ጀርመን አገር በሚገኘው የሌፕዥግ ከተማ የስዕል ውድድር ተሳትፈዋል።

May be an image of 2 people, people standing and outdoors

በውድድሩ ሁለቱ ኢትዮጵያውያን የአንደኛና የሁለተኛ ደረጀ ይዘው ማጠናቀቃቸውን የአዲስ አበባ ቴክኒክ ሙያ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ ቢሮ አስታውቋል፡፡

ቢሮው እንዳለው ውድድሩ የአዲስ አበባ እህት ከተማ በሆነችው ሌፕዥግ ከተማ የተካሄደ ሲሆን የሁለቱን ከተሞች እህትማማችነት ሊያሳይ በሚችል የኪነ ቅርፅ ውድድር ከ25 ልምድ ካላቸው ሰዓሊያን ጋር በመወዳደር አንደኛና ሁለተኛ በመውጣት አሸናፊ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

May be an image of 2 people
May be an image of 2 people

ሠልጣኝ ፍሬወይኒ እንድሪያስ እና እዮብ እሸቱ እንደ ቅድመ ተከተላቸው አንደኛ እና ሁለተኛ በመውጣት አሸናፊ የሆኑበትን ሽልማት ተቀብለዋል።

የህይወት ተሞክሯቸውንና የወደፊት ራዕያቸውን በቦታው ላይ ለተገኙ ታዳሚያን ያቀረቡ ሲሆን በውድድሩ አንደኛ የወጣችው ሰልጣኝ ፍሬወይኒ የሶስት ወር ነፃ የትምህርት ዕድል እንደተሰጣት ተገልጿል።

ከዓለም አቀፍ ሰዓሊያን ጋርም ስራዎቿን እንድታቀርብ የሌፕዥግ ከተማ አስተዳደር ዕድሉን ያመቻቸላት መሆኑን ለመረዳት ተችሏል።

በውድድሩ አሸናፊ የሆነው ኪነ ቅርፅም የአዲስ አበባ እህት ከተማ በሆነችው ሌፕዥግ በሚገኘው የአዲስ አበባ አደባባይ ተብሎ በተሰየመው ቦታ ላይ የሚተከል ይሆናል ነው የተባለው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም