የሀዋሳ ዪኒቨርስቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለ17ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን የህክምና ባለሙያዎች እያስመረቀ ነው

97

ሀዋሳ መስከረም 15/2015 (ኢዜአ) የሀዋሳ ዪኒቨርስቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለ17ኛ ጊዜ በተለያዩ የህክምና ሙያ ያሰለጠናቸውን 421 ተማሪዎች እያስመረቀ ነው።

ከተመራቂዎች መካከል 11 ዱ በሜዲካል ራዲዮሎጂ ድህረ ምረቃ እና 157ቱ ደግሞ የህክምና ዶክተሬት ተመራቂዎች መሆናቸውን የኮሌጁ ዳይሬክተር ተወካይ ኡርጌሳ ዋርሳሞ ለኢዜእ ገልፀዋል።

ቀሪዎቹ በመጀመሪያ ድግሪ ጤና ሞኮንን፣ አዋላጅ ነርስና በሌሎች የህክምና ሙያዎች በመደበኛው መርሃ-ግብር ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።

ከ17ኛው ዙር ተመራቂዎች መካከል 130 ዎቹ ሴቶች መሆናቸውንም ተወካዩ ጠቅሰዋል።

በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አየለ ተሾመ፣ የፌዴራልና የክልል የስራ ሃላፊዎች፣ የዪኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮችና መምህራን እንዲሁም የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም