በድንገተኛ እሳት አደጋ ቤታቸው የተቃጠለባቸው የዘጠኝ አቅመ ደካማ ወገኖች የመኖሪያ ቤት እድሳት ተጠናቆ በዛሬው እለት ለነዋሪዎቹ ተላለፉ

120

መስከረም 15 /2015 (ኢዜአ)በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በድንገተኛ እሳት አደጋ ቤታቸው የተቃጠለባቸው የዘጠኝ አቅመ ደካማ ወገኖች የመኖሪያ ቤት እድሳት ተጠናቆ በዛሬው እለት ለነዋሪዎቹ ተላለፉ።

የቤቶቹ እድሳቱም የተከናወነው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ፅህፈት ቤት ከኤምሲጂ ኮንስትራክሽን ጋር በመተባበር መሆኑን ለማወቅ ተችሏል ።

May be an image of 7 people, people sitting, people standing and outdoors

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የመኖሪያ ቤቱን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዘጠኝ በመገኘት ለነዋሪዎቹ አስረክበዋል።

ከተማ አስተዳደሩ በመዲናዋ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎችን ፍትሃዊ በሆነ መልኩ አጠናክሮ ይሰራል ብለዋል።

May be an image of indoor

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በ2013 ዓመተ ምህረት በድንገተኛ እሳት የመኖሪያ ቤቶቹ ቃጠሎ እንደደረሰባቸው ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም