በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የደመራና የመስቀል በዓላት በሠላም እንዲከበሩ ዝግጅት ተደርጓል- ፖሊስ - ኢዜአ አማርኛ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የደመራና የመስቀል በዓላት በሠላም እንዲከበሩ ዝግጅት ተደርጓል- ፖሊስ
150
ሚዛን አማን፣ መስከረም 14 ቀን 2015 (ኢዜአ) የደመራ እና መስቀል በዓላት በሰላም እንዲከበሩ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ነብዩ ኢሳያስ ለኢዜአ እንደገለጹት ለበዓሉ ዝግጅት በክልሉ ስድስት ዞኖች የሚገኙ የጸጥታ መዋቅሮች በጋራ እየሰሩ ነው።
ሕብረተሰቡ ከጸጥታ አካላት ጎን በመቆም በዓሉ በሰላም እንዲከበር የተለመደውን ትብብር እንዲያደርግ ጥይቀዋል።
ነዋሪዎች በበዓል ወቅት አጠራጣሪ ሁኔታዎችን ሲመለከቱ ለፖሊስ ጥቆማ እንዲሰጡም ነው ያመለከቱት።