የገንዘብ ሚኒስትሩ በኢትዮ- ጅቡቲ ስታንደርድ ጌጅ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ስብሰባ ላይ ለመታደም ድሬዳዋ ገቡ

87

ድሬደዋ፤ መስከረም 13/2015(ኢዜአ) ፡- የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ በኢትዮ- ጅቡቲ ስታንዳርድ ጌጅ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ስብሰባና ሌሎች መረሃ ግብሮች ላይ ለመታደም ዛሬ ድሬዳዋ ገቡ።

በስብሰባው  የአክሲዮን ማህበሩ የቦርድ አመራሮች በቆታቸው የድርጅቱን አፈጻጻም ይገመግማሉ፤ የሀይል አቅርቦት፣ የፀጥታና አደረጃጀት ጉዳዮችን በስፋት እንደሚዳሰሱ ይጠበቃል።

በተጨማሪም ከሁለቱ ሀገራት የተወከሉ የቦርድ አባላትና የፀጥታ ዘርፍ ሃላፊዎች የባቡር ዘርፍ አቅም ግንባታ ስራ የደረሰበትን ደረጃ ምልከታ እንደሚያደርጉ ተመልክቷል።

የኢትዮ-ጅቡቲ ስታንደርድ ጌጅ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑን የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ድሬዳዋ ኢንተርናሽናል አውራፕላን ማረፊያ  ሲደርሱ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ፣ የቦርዱ አመራር አባላት እና ሌሎች አመራሮች  አቀባበል አድርገውላቸዋል።

መረሃ ግብሮቹ  እስከ መስከረም 16/2015 ዓ.ም የሚቆይ መሆኑን የኢዜአ ሪፖርተር ከድሬዳዋ  ዘግቧል።