35ኛው ሀገር አቀፉ የቱሪዝም ቀን በአሶሳ እየተከበረ ነው

91

አሶሳ መስከረም 13 / 2014 (ኢዜአ) 35ኛው ሀገር አቀፉ የቱሪዝም ቀን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ እየተከበረ ነው።

የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕስ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰን እና ሌሎችም ከፍተኛ አመራሮች በዝግጅቱ ላይ እየተሳተፉ ነው።

በዝግጅቱ ሚኒስትሯ እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ አመራሮች ቱሪዝምን የማጠናክሩ መልዕክቶች እንደሚተላለፉ ይጠበቃል።

በአካባቢው የሚገኙ ባህላዊ፣ ታሪካዊና ተፈጥሯዊ ሃብቶች የሚጎበኙ ሲሆን የዘርፉን ሀብቶች በሚገባ ማልማት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግ ተመልክቷል።

ለ35ኛ ጊዜ የሚከበረው የዘንድሮ የቱሪዝም ቀን መሪ ሀሳብ "አዲስ እሳቤ ለቱሪዝም" በሚል እስከ መስከረም 15 / 2015 ዓ.ም እንደሚቀጥል የኢዜአ ሪፖርተር ከሥፍራው ዘግቧል።  

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም