አሸባሪው ህወሓት "ሰላም" የሚለው ጊዜ በመግዛት ጦርነቱን ለማራዘም ነው - አምባሳደር ፍጹም አረጋ

163

መስከረም 7 /2015 (ኢዜአ) አሸባሪው ህወሓት "ሰላም" የሚለው ጊዜ ገዝቶ ጦርነቱን የማራዘም ፍላጎት ስላለው ነው ሲሉ በካናዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ ገለጹ።

የሽብር ቡድኑ ከዚህ ቀደም መንግስት ያወጃቸውን የተኩስ አቁሞችና ያቀረበውን የሰላም ጥሪ “ጦርነቱን አሸንፊያለሁ” በሚል ማጣጣሉንና ውድቅ ማድረጉን አምባሳደር ፍጹም በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ ገልጸዋል።

ቡድኑ በለመደው የስርቆት ተግባሩ በመቀጠል ለሰብአዊ እርዳታ የሚውል ከ500 ሺህ ሊትር በላይ ነዳጅ መዝረፉን አመልክተዋል።

አሸባሪው ቡድን በአፍራሽ ተግባሩ ቢቀጥልም የኢትዮጵያ መንግስት ለሰላም የዘረጋውን እጅ አላጠፈም ብለዋል።

“የሽብር ቡድኑ ከሰሞኑ ሰላም እፈልጋለሁ በሚል ያወጣው መግለጫ ጊዜ መግዣና ራሱን ለጦርነት የማዘጋጃ አካሄድ ነው” ያሉት አምባሳደር ፍጹም “ይህ የቡድኑን እብሪት” የሚያሳይ መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም