ዋልያዎቹ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከኬንያ ጋር ለሚያደረጉት ጨዋታ 26 ተጫዋቾች ጥሪ ተደርጓላቸዋል

65
አዲስ አበባ መስከረም 9/2011 የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዋልያዎቹ ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከኬንያ ጋር ለሚያደረገው ጨዋታ ለ 26 ተጫዋቾች ጥሪ ተደርጓል። በአሰልጣኝ አብርሃም  መብራቱ የሚመሩት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሄራዊ ቡድን /ዋልያዎቹ/  እ.አ.አ በ2019 በካሜሮን አስተናጋጅነት በሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ለመሳተፍ የማጣሪያ ጨዋታቸውን እያደረጉ ይገኛሉ። በዚህ መሰረትም የምድቡን ሶስተኛ የማጣሪያ ጨዋታቸውን  መስከረም 30 ቀን 2011 ዓ.ም በባህርዳር  ስታዴየም ከኬንያ አቻቸው ጋር ያከናውናሉ። ለዝግጅቱ በሀገር ውስጥ ሊግ የሚጫወቱ  22 ተጫዋቾችና በውጭ ሀገራት የተለያዩ ሊጎች  የሚጫወቱ አራት ተጫዋቾች ተካተዋል። ከኬንያ ጋር ለሚደረገው ለዚህ ጨዋታ ከቅዱስ ቅዮርጊስ ሳልሃዲን ባርጌቾ፣ አቤል ያለው ፣አስቻለው ታመነ፣አብዱልከሪም መሃመድ፣ሄኖክ አዱኛ፣በሃይሉ አሰፋ፣ናትናኤል ዘለቀ፣ጌታነህ ከበደ እና ሙሉዓለም መስፍን ተመርጠዋል። ከኢትዮጵያ ቡና ደግሞ አህመድ ረሺድ፣አማኑኤል ዮሐንስ፣ተመስገን ካስትሮ ሲመረጡ ከአዳማ ከተማ ደግሞ ከነዓን ማርክነህና ዳዋ ሁቴሳ፣ ከድሬዳዋ ከተማ አንተነህ ተስፋዬና ሳምሶን አሰፋ ለዚህ ጨዋታ ጥሪ ተደርጎላቸዋል። ከፋሲል ከተማ አምሳሉ ጥላሁን፣ሽመክት ጉግሳና ሙጂብ ቃሲም ሲጠሩ ከሀዋሳ ከተማ ተክለማሪየም ሻንቆ፣  ከአርባ ምንጭ ከተማ ጽዮን መርእድ ከሲዳማ ቡና አዲስ ግደይ ጥሪ ከተደረገላቸው ተጫዋቾ መካከል ተካተዋል። በውጭ ሊግ ከሚጫወቱ ተጫዋቾች ኡመድ ኡክሪ ከግብጽ ስሞሀ ፣ሽመልስ በቀለ ከግብጽ ፔትሮጀት ክለብ ፣ጋቶች ፓኖም  ከግብጹ ኤልጎውና  ቢኒያም በላይ ከአልባኒያ ሰከንደርቡ ኮርሲ ክለብ ለብሄራዊ ቡድኑ ጥሪ የተደረገላቸው  ናቸው። ለዚህ ጨዋታ ዝግጅትም ከመስከረም 20 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ በሆቴል ተሰባስበው ዝግጅታቸውን የሚያደረጉ ይሆናል። ዋልያዎቹ እ.አ.አ በ2019 የካሜሮን የአፍሪካ ዋንጫ  ለመሳተፍ በማጣሪያው ከጋና፣ ኬንያና ሴራሊዮን ጋር ተደልድለው የማጣሪያ ጨዋታቸውን እያደረጉ ይገኛሉ። እስካሁንም ባደረጓቸው  ሁለት ጨዋታዎች ሁሉም ሀገራት ሶስት ነጥብ ይዘው በጎል ክፍያ ብቻ ተበላልጠው ከአንደኛ እስከ አራተኛ ደረጃ ተቀምጠዋል።        
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም