ዶክተር ዊሊያም ሩቶ የኬንያ 5ኛው ፕሬዚደንት በመሆን ቃለ-መሃላ ፈጸሙ

331

መስከረም 3 /2015 (ኢዜአ) ዶክተር ዊሊያም ሩቶ ይፋዊ የኬንያ ፕሬዚደንት የሚያደርጋቸውን ቃለ-መሃላ በመፈጸም ፕሬዚደንትነታቸው ታወጀ፡፡

አዲሱ የኬንያ ፕሬዚደንት ዶክተር ዊሊያም ሩቶ ቃለ-መሃላ ካከናወኑ በኋላ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በተመሳሳይም በምክትል ፕሬዚደንትነት የተመረጡት ሪጋቲ ጋቻጉዋ ቃለ-መሃላ በመፈጸም ስልጣናቸውን በይፋ ተረክበዋል፡፡

በበዓለ ሢመቱ ላይ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የበርካታ ሀገራት መሪዎችና ዲፕሎማቶች ታድመዋል፡፡