25 የመንግስት ተቋማት 326 አገልግሎቶችን በኦንላይን እየሰጡ ነው--የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር

123

ጳጉሜን 3 / 2014 (ኢዜአ)25 የፌደራል መንግስት ተቋማት 326 አገልግሎቶችን በኦንላይን አማካይነት ለማህበረሰቡ እየሰጡ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለጸ።

የሚኒስቴሩ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ነገ የሚከበረውን የአገልጋይነት ቀን በማስመልከት በሰጡት መግለጫ ቀኑ "አገልጋይነት ከእኔ ይጀምራል" በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ ዝግጅቶች ታስቦ እንደሚውል ጠቁመዋል።

ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ዜጎች ባሉበት ሆነው በኢ-ሰርቪስ አማካይነት ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በዕለቱም በኤሌክትሮኒክስ አገልግሎት ሁሉንም ዜጎች በእኩልነት ተደራሽ ለማድረግ የተጀመሩ እንቅሰቃሴዎችን የሚያጠናክሩ ተግባራት እንደሚከናወኑ ነው የተናገሩት።

25 የፌደራል መንግስት ተቋማት ከሚኒስቴሩ ጋር በመተባበር በኢ-ሰርቪስ ስርዓት የአንድ መስኮት ቀልጣፋ አገልግሎትን እየሰጡ መሆኑን እንዲሁ።

በዚህም ህብረተሰቡ ባለበት ቦታ ሆኖ 326 አይነት አገልግሎቶችን በኦንላይን እንዲያገኝ መደረጉን አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም