የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል የቡራዩና አካባቢው ተፈናቃዮችን እየጎበኙ ነው

60
አዲስ አበባ መስከረም 9/2011 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል በቡራዩና አካባቢው በተፈጸመ ጥቃት ተፈናቅለው በፊሊጶስና በብስራት ትምህርት ቤት የሚገኙ ተፈናቃዮችን እየጎበኙ ነው። አፈ ጉባዔዋ ተፈናቃዮቹ ተጠልለው በሚገኙባቸው ሁለቱ ትምህርት ቤቶች ተገኝተው ህጻናትን፣ እናቶችን፣ ወጣቶችንና አዛውንቶችን ጎብኝተዋል፤ በቅርበትም አነጋግረዋል። መንግስት ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ጥረት እያደረገ መሆኑን የገለጹት አፈ ጉባዔዋ፤ ጥቃት ያደረሱ አካላትን ተጠያቂ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል። ተፈናቃዮች ወደቀያቸው እንዲመለሱ እየተሰራ እንደሆነ ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም