የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች በቡራዩና አካባቢው በተፈጸመ ጥቃት ለተፈናቀሉ ዜጎች የ350 ሺህ ብር ድጋፍ አደረጉ

69
አዲስ አበባ መስከረም 9/2011 በአዲስ አበባ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች በቡራዩና አካባቢው በተፈጸመ ጥቃት ለተፈናቀሉ ዜጎች ከ350 ሺህ ብር በላይ የሚገመት የምግብ፣ አልባሳትና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ። የክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ስንታየሁ መለሰ ለኢዜአ እንዳስታወቁት፤ ነዋሪዎቹ ለተፈናቃዮች ድጋፍ ለመስጠት በተቋቋመው ኮሚቴ አማካኝነት ከ1 ሺህ 200 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ነው የምግብ፣ የአልባሳትና ቁሳቁስ ድጋፍ ያደረጉት። የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ከቡራዩና ሌሎች የአዲስ አበባ ዙሪያ ከተሞች ተፈናቅለው በተለያዩ ትምህርት ቤቶች የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው ቀጥለዋል ተብሏል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም