የአፍሪካ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ 2022 በአዲስ አበባ ተከፈተ

82

ጷጉሜን 2/2014/ኢዜአ/ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ምርትና አገልግሎታቸውን የሚያስተዋውቁበት "የአፍሪካ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ 2022" በአዲስ አበባ ተከፈተ።

ኤክስፖው ለልምድ ልውውጥ እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተጠቅሷል፡፡

ከጷጉሜ 2 እስከ 4 ቀን 2014 ዓ.ም የሚቆየው ኤክስፖ አፍሪካ ለጀመረችው ነፃ የንግድ ቀጠና እውን መሆን የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣም ነው የተገለጸው፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላ በመርሐ ግብሩ ላይ እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ የአምስት ዓመት የዲጂታል ስትራቴጂ  በመቅረጽ ዘርፉ ለኢኮኖሚው ልማት ያለውን እድል ለመጠቀም እየሰራች ስለመሆኑ ተናግረዋል፡፡

ኤክስፖው ስራ ፈጣሪ ወጣቶችን ለማፍራት ሚናው የጎላ መሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡

የኢትዮጵያን ገጽታ ለማስተዋወቅ እንደሚጠቅምም እንዲሁ፡፡

በኤክስፖው በተለያየ ርዕሰ ጉዳዮች ሲምፖዚየሞች የሚካሄዱ ሲሆን፤ ትልልቅ ኩባንያዎች፣ የፈጠራ ባለተሰጥኦዎች፣ በአይሲቲ ዘርፍ የተመረጡ ቴክኖሎጂዎች፣ የሮቦት፣ ስታርታፖችን፣ የቴክኖሎጂ ዕድገትን ማቀድ የሚያስችሉ አሠራሮችን ማሳየት የሚያስችሉ አጋጣሚዎችን የፈጠረ መሆኑም ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም