ለህዝባችን ሰላምና እድገት ከምንጊዜም በላይ ጠንክረን እንሰራለን--- የኦህዴድ ምክትል ሊቀመንበር

87
መስከረም 8/2011 ለህዝቡ ሰላምና እድገት  ከምንጊዜም በላይ ጠንክሮ መስራት እንደሚገባ   የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንትና የኦህዴድ ምክትል ሊቀመንበር  ለማ መገርሳ ተናገሩ፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት/ኦህዴድ/ 9ኛ ጉባኤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳና  ከ7 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች  በተገኙበት ዛሬ በጅማ ከተማ  ተጀምሯል። በጉባኤው መክፈቻ ላይ የኦህዴድ ምክትል ሊቀመንበርና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ  እንደተናገሩት  ብዙ ውጣ ውረድን በማለፍ  የመጣውን ለውጥ ለማደናቀፍ ዛሬም ጥረት እያደረጉ ያሉ ቡድኖችና ግለሰቦች እንዳሉም ጠቁመዋል፡፡ እርስ በራሳችን ተጨማሪ ሀይልና ጉልበት መሆን  ይገባናል ያሉት ፕሬዝዳንቱ  ህዝቡ ታግሎ ያመጣውን ድል ይፋ በማድረግ መሰረት ጥሎ እንዲቆምና ለስኬት እንዲበቃ  ህዝቡ በአንድነት ጠንክሮ እንደሚሰራ ከፍተኛ እምነት አለኝም በአንድነት ሆኖ በጋራ በመሰለፍ፣ በመደማመጥ፣ በመከባበርና በመስማማት ጠንክረን መስራት ለትግላችን ስኬታማነት ወሳኝ ነው  ብለዋል፡፡ ባለፉት ጊዜያት መከፋፈልና  አንድነት ማጣት የኦሮሞን ትግል ወደ ኃላ አስቀርቷል ያሉት አቶ ለማ  መስማማት ባሉባቸው ትላልቅ ጉዳዮች ላይ ተስማምቶ በመስራት፣ ባልተስማሙት  ጥቃቅን ነገሮችን  ላይ ደግሞ በመወያየት እየፈቱ  ወደ ፊት መራመድ ወሳኝ  መሆኑን ገልፀዋል።            
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም