በቡራዩና አካባቢው በደረሰው የዜጎች ህይወት መጥፋትና መፈናቀል ማዘኑን የጋምቤላ ክልል አስታወቀ

89
ጋምቤላ መስከረም 9/2011 በአዲስ አበባ ቡራዩ አካባቢ ሰሞኑን በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋትና የዜጎች መፈናቀል ጥልቅ ሐዘን የተሰማው መሆኑን የጋምቤላ ህዝቦች ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ገለጸ። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሰናይ አኩዎር ለኢዜአ እንደገለጹት በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ በፍቅር እንደመር፤ በይቅርታ እንሻገር በሚል እሳቤ የተገኘውን ለውጥ ቀጣይነት ለማረጋገጥ እየተሰራ ባለበት ወቅት ይህን መስል ጉዳት መፈጠሩ የሚያሳዝን ተግባር ነው። "በግጭቱ በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት፣ የአካል ጉዳት፣ የንብረት ውድመትና የዜጎች መፈናቀል የክልሉን ህዝብና መንግስት በእጅጉ አሳዝኗል" ብለዋል ። "ችግር ፈጣሪዎች በሀገሪቱ የመጣውን ለውጥ ለማሰናከል አስበው ከሆነ ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ ይገባል" ያሉት ምክትል ርዕስ መስተዳዱሩ ለውጡ በህዝብ ግፊት የመጣ ስለሆነ በማንም ሊቀለበስ እንደማይችል አረጋግጠዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም