የኢትዮጵያን ምርታማነት ለማሳደግ የተቋማት ቅንጅታዊ ስራ መጠናከር አለበት

137

አዲስ አበባ ጳጉሜን 1/2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያን ምርታማነት ለማሳደግ የተቋማት ቅንጅታዊ አሰራር መጠናከር እንዳለበት የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

ነገ የሚከበረውን ”የአምራችነት" ቀን በተለያዩ መርሃ ግብር ስድስት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በጋራ ለማክበር መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።

የእለቱን መርሃ ግብር በማስመልከት የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር፣ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር፣ የማዕድን ሚኒስቴር፣ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴርና የግብርና ሚኒስቴር በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ጉዳዮች ዳይሬክተር አበባ ታመነ፤በ”ኢትዮጵያ ታምርት” ሀገራዊ ንቅናቄ የምረትና የውጭ ምንዛሬ ግኝት የላቀ ውጤት መገኘቱን አስታውቀዋል።

በሂደቱ ምርታማነትን ከማሳደግ ባለፈ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች እውን ስለመሆናቸው ጠቅሰው የተገኘውን ውጤት ለማስቀጠል የተቋማት ቅንጅታዊ ስራ መጠናከር አለበት ብለዋል።

የአምራችነት ቀን ከተለያዩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ጋር በነገው እለት በተለያዩ መርሃ ግብሮች የሚከበር መሆኑን አመላክተዋል።

እለቱን በማስመልከት ኤግዚብሽንና ባዛር እንደሚዘጋጅ ጠቁመው ተመሳሳይ መርሀ ግብሩ በክልሎችም ይከናወናል ብለዋል።

በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የሕዝብ  ግንኙነትና  ኮሙኒኬሽን  ጉዳዮች  ሥራ አስፈጻሚ ታጠቅ ነጋሽ የትራንስፖርት አገልግሎት በተሟላ መልኩ የሚቀርብ መሆኑን ገልጸው በመርሃ ግብሩ ላይ ህብረተሰቡ እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም