ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ከአልጀሪያ ፕሬዝዳንት አብዱልመጅድ ታቡኔ ጋር ተወያዩ

111

ነሐሴ 23 ቀን 2014 (ኢዜአ) በአልጀሪያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከአልጀሪያው ፕሬዝዳንት አብዱልመጅድ ታቡኔ ጋር ተወያዩ።

ሁለቱ መሪዎች በተለይም የኢትዮጵያ እና አልጀሪያን የረጅም ጊዜ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ምክክር አድርገዋል።የሁለቱን አገራት የኢኮኖሚ ትስስር ለማጎልበት በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይም ተወያይተዋል።

በአልጀሪያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፤ ከፕሬዝዳንት አብዱልመጅድ ጋር ከመወያየታቸው ቀደም ብለው በአልጀርስ የሚገኘውን ሳይዳል የመድሃኒት ፋብሪካ ጎብኝተዋል።

በአፍሪካም በግዙፍነቱ የሚጠቀሰው ሳይዳል የመድሃኒት ፋብሪካ ከተመሰረተ 40 ዓመታትን ያስቆጠረ፤ ከ200 በላይ የመድሃኒት ዓይነቶችን የሚያመርት ሲሆን በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ መድሃኒት የመላክ እቅድ አለው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም