ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአልጀርስ የሚገኘውን ሳይዳል የመድሃኒት ፋብርካን ጎበኙ

114

ነሀሴ 23/20214 /ኢዜአ/ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በአልጀርስ የሚገኘውን ሳይዳል የመድሃኒት ፋብሪካን ጎብኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰሜን አፍሪካዊቷ አልጀሪያ ከትናንት ጀምሮ ይፋዊ ጉብኝት እያደረጉ ነው።

በዛሬው ዕለትም በሀገሪቱ ዋና ከተማ የሚገኘውን ሳይዳል የመድሃኒት ፋብሪካን ጎብኝተዋል።

ከተመሰረተ 40 ዓመታትን ያስቆጠረው ፋብሪካው 200 የመድሃኒት ዓይነቶችን በማምረት ላይ  የሚገኝና በአፍሪካም በግዙፍነቱ የሚጠቀስ ነው።

አፍሪካን በመድሃኒት የማስተሳሰር እቅድ ይዞ እየሰራ መሆኑንም የፋብሪካው አመራሮች ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገልጸውላቸዋል።

በቅርቡም ወደ ኢትዮጵያ መድሃኒት መላክ እንደሚጀምር  ተጠቁሟል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአልጀሪያ እያደረጉት ባለው ይፋዊ የስራ ጉብኝት በርእሰ መዲናዋ አልጀርስ የሚገኘውን የሰማዕታት መታሰቢያ ሙዚየምን በመጎብኘት በስፍራው የአበባ ጉንጉን አኑረዋል።

በአልጀሪያ ቆይታቸው ከሀገሪቱ ፕሬዝዳንት አብዱል መጅድ ታቡኔ ጋር በመገናኘት የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በሚጠናከርባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም