አቶ ኢሳያስ ጅራ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሆነው በድጋሚ ተመረጡ

321

ነሐሴ 22 ቀን 2014 (ኢዜአ) አቶ ኢሳያስ ጅራ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሆነው በድጋሚ ተመረጡ።

በቀጣይ አራት አመታት ፌዴሬሽኑን ለማገልገል በፕሬዚዳንትነት የተመረጡት አቶ ኢሳያስ ከተፎካካሪዎቻቸው በሰፊ የድምጽ ብልጫ በማግኘት ነው።

አቶ ኢሳያስ ጅራ 94፣ አቶ መላኩ ፈንታ 27 እንዲሁም ኢንጂነር ቶክቻ አለማየሁ 17 ድምጽ አግኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም