አራተኛው ዙር አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ማጠቃለያ ተካሄደ

166

ነሐሴ 22 ቀን 2014 (ኢዜአ) አራተኛው ዙር አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ማጠቃለያ በዱከም ከተማ ተካሄደ ።

መርሀ ግብሩ የተካሄደው በግብርና ሚኒስቴር፣ የኦሮሚያ ግብርና ቢሮና ዱከም ከተማ አስተዳደር በጋራ በመሆን ነው ።

No photo description available.

በማጠቃለያው ስነ-ስርአት ላይ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች፣አባ ገዳዎችና ሀደ ሲንቄዎች እንዲሁም አርቲስቶች ተገኝተው በዱከም ሲቲ ፓርክ ውስጥም ችግኞችን ተክለዋል።

የዱከም ከተማ ከንቲባ አቶ አብዱጀሊል አብድሮ እንደተናገሩት በኢትዮጵያ ባለፉት ተከታታይ አራት ዓመታት ውጤታማ የአረንጓዴ አሻራ ልማት ተካሂዷል ።

ይህም የአየር ንብረት ለውጥን በመቋቋም ረገድ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።

በከተማ ደረጃ በአራተኛው ችግኝ ተከላ መርሀግብር ከ3 ሚሊዮን በላይ ችግኞች ተተክለዋል ነው ያሉት ።

ዱከም የኢንዱስትሪ ከተማ ከመሆን ባለፈ በአረንጓዴ አሻራ ልማት አርአያ ከተማ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል ።

May be an image of 3 people

የዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ አስተባባሪ ሚኒስትር ዶክተር አለሙ ስሜ በበኩላቸው አረንጓዴ አሻራ ልማትና ብልጽግናን ለማረጋገጥ የላቀ ድርሻ አለው ብለዋል ።

ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለች አገር ለማስረከብ የችግኝ ተከላው መርሃግብር መሰረት መሆኑንም አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም