የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በበጀት አመቱ 55 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ገለጸ

123

ነሃሴ 13/2014/ኢዜአ/ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በ2014 በጀት አመት 55 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ገለጸ።

ቢሮው የ2014 በጀት አመትና በ2015 በጀት አመት እቅድ ላይ ውይይት እያካሄደ ይገኛል።

በ2014 በጀት አመት 48 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 55 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ እንደተቻለ ተገልጿል።

የእቅድ አፈጻጸሙ የ7 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ብልጫ ያለው መሆኑ ተነግሯል።

አፈጻጸሙ ከ 2013 በጀት አመት ጋር ሲነጻጸር በ13 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር እድገት ያሳየ ነው ተብሏል።

አዳዲስ የአሰራር ስርዓቶች ተግባራዊ መደረጉ፣ በቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች መካከል የትብብርና ፉክክር መንፈስ እንዲጠናከር መደረጉ፣ የህግ ማስከበር አቅም እየተሻሻለ መምጣቱ ቢሮው ላስመዘገበው ውጤት አገዛ አድርጓል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም