ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ዓላማ እንዲሳካ የክልሉ መንግስት ድጋፍ ያደርጋል -የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር

93

ሐረር፤ ነሐሴ 12/2014(ኢዜአ) ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ዓላማ እንዲሳካ የክልሉ መንግስት ሁለንተናዊ ድጋፍ እንደሚያደርግ የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሚስራ አብደላ አስታወቁ።

ኮሚሽኑ ከሐረሪ ክልል አመራር እና ባለድርሻ አካላት ጋር የትውውቅ  ፕሮግራም እያካሄደ ነው።

በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሯ ባደረጉት ንግግር ፤  ኮሚሽኑ የያዘው ዓላማ ኢትዮጵያዊያንን የጋራ አሸናፊ የሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል።

ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ኢትዮጵያዊያን  አሳታፊና  በመግባባት  በራሳቸው  ጉዳይ  መክረው መፍትሔ እንዲያስቀምጡ የሚያግዝ በመሆኑ ይህ  እንዲሳካ  የክልሉ መንግስት ሁለንተናዊ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል፡፡

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ኢትዮጵያን ካለችበት ችግር ያወጣል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት መሆኑን የገለጹት ደግሞ ሌላው በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት  አምባሳደር መሐሙድ ዲሪር ናቸው።

በክልሉ ምክር ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ እየተካሄደ ያለው የኮሚሽኑ  የትውውቅ ፕሮግራም የኮሚሽኑ የህግ ማዕቀፍና የተጓዘበትን ሂደት  መነሻ  ሀሳብ ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግ ይጠበቃል።

በዚህም  የኮሚሽኑ ፣ የክልሉ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ነው።

ኮሚሽኑ ተጠሪነቱ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት  ሲሆን በርካታ የማህበረሰብ ክፍሎችና ባለድርሻ አካላት  እንዲወያዩበት እየተደረገ መሆኑን በትውውቅ ፕሮግራሙ ላይ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም