ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት የተከናወነውን የህንፃ ማስፋፊያና የሸበሌ ወረዳ ዘመናዊ የግመል እርባታ የስራ እንቅስቃሴ ጎበኙ

81

ነሐሴ 8 ቀን 2014 (ኢዜአ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት የተከናወነውን የህንፃ ማስፋፊያና በሸበሌ ወረዳ በአንድ ባለሀብት የሚካሄደውን ዘመናዊ የግመል እርባታ የስራ እንቅስቃሴ ዛሬ ጎበኘተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት የክልሉ መንግስት ቀደም ሲል ለእርሻ ልማት ያልዋሉ ተስማሚ መሬትን ለእርሻ ስራ እንዲዉሉ ትኩረት መሰጠቱን አድንቀዋል።

በክልሉ እየለማ ያለው ሰብል የገበያ ትስስር በመፍጠር ረገድ በድሬዳዋ የተጀመረው ንጻ የንግድ ቀጠና የጎላ ጠቀሜታ ይኖረዋል ብለዋል።
የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ በክልሉ "ባለፉት አመታት ይገኝ የነበረው ምርት 10 ሚልየን ኩንታል እንደነበር ገልጸው በዘንድሮው የእርሻ ልማት ስራ ትኩረት በመስጠት ከተለያዩ ሰብሎች ወደ 28 ሚልየን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተመራው ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች መካከል የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደን ፋራህ ይገኙበታል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በጅግጅጋና ፋፈን ዞን ቆይታቸውን በቱሊ ጉሌድ ኩሉላ ቀበሌ እየለማ ያለው ኩታ ገጠም የስንዴ ማሳንም ጎብኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው እለት በድሬደዋ ከተማ በመገኘት አራተኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በስኬት መከናወኑን ይፋ ያደረጉ ሲሆን የድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጣናን መርቀው መክፈታቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም