እየገነባናቸው ያሉት ነፃ የንግድ ቃጣናዎች በፍጥነት እየተለወጠ ወደሚገኘው ዓለም የምንቀላቀልባቸው መንገዶቻችን ናቸው-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

191


ነሐሴ 8 ቀን 2014 (ኢዜአ)እየገነባናቸው ያሉት ነፃ የንግድ ቃጣናዎች በፍጥነት እየተለወጠ ወደሚገኘው ዓለም የምንቀላቀልባቸው መንገዶቻችን ናቸው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጣናን መርቀው በከፈቱበት ወቅት እንደገለጹት፤በተለመደው መንገድ እየተጓዝን የሀገራችንን የኢኮኖሚና የቴክኖሎጂ አቅም ማሳደግ አዳጋች ነው።
አዲስና ፈጠራ የታከለባቸው መንገዶችን መከተል ይኖርብናል።ዓለም በእጅጉ እየተቀየረ ነው ያሉት።
በቀድሞ አስተሳሰብ አዲሱን ዓለም ለመቀበል መሞከር ልጆቻችንን በሕጻንነታቸው ባዘልንበት ጫንቃችን በወጣትነታቸው ለማዘል እንደመሞከር ይቆጠራል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ዞኖቹ ንግድና ኢንቨስትመንትን ከማቀላጠፍ ባለፈ የቴክኖሎጂ አቅማችንን እንደሚያሳድጉ አልጠራጠርም ማለታቸው ከማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም