ከአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የተመረቁ ደቡብ ሱዳናውያን ተማሪዎች ኢትዮጵያ የአፍሪካ ድምጽ ናት ሲሉ ገለጹ

276

ነሐሴ 07 ቀን 2014 (ኢዜአ) “ኢትዮጵያ አሁንም የአፍሪካ ድምጽ ናት” ሲሉ ከአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ የተመረቁ ደቡብ ሱዳናውያን ተማሪዎች ገለጹ።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ጠንካራ ማነንት ያላቸው ሕዝቦች አገር ናት ብለዋል።

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ በቅደመ እና ድህረ ምረቃ ያስተማራቸውን 1 ሺህ 132 ተማሪዎች አስመርቋል።

ከተመራቂዎቹ መካከል የሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሩዋንዳ፣ ኮንጎ እና ሌሎችም አገራት ዜጎች ይገኙበታል፡፡

ኢዜአ ያነጋገራቸው ደቡብ ሱዳናውያን ተመራቂዎች ኢትዮጵያ በሁሉም መስክ ለአፍሪካ ኩራት ናት ብለዋል።

ኢትዮጵያ ወትሮም የአፍሪካ ድምጽ፣ በአፍሪካ በቅኝ ያልተገዛች ሀገር እንዲሁም የሰው ዘር መገኛ ናት ሲሉ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ለውጥ ድጋፍ እያደረገች መሆኑንና የኢትዮጵያ መንግስት እና ሕዝብ ለደቡብ ሱዳን መረጋጋት ወሳኝ አበርክቶ እንዳላት አመልክተዋል።

ተመራቂዎቹ ወደ አገራቸው ሲመለሱ የኢትዮጵያና የደቡብ ሱዳንን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ስራ እንደሚያከናውኑ አረጋግጠዋል።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ይዛ በርካታ ስደተኞች የምታስተናግድ መሆኗ ከሌሎች አገራት ልዩ ያደርጋታልም ብለዋል።