ኢትዮጵያ ፈተናዎችን በብቃት እያለፈች ወደ ብልጽግና የጀመረችውን ጉዞ ትቀጥላለች-አቶ ኦርዲን በድሪ

171

ነሐሴ 5 ቀን 2014 (ኢዜአ) ኢትዮጵያ ፈተናዎችን በብቃት እያለፈች ወደ ብልጽግና የጀመረችውን ጉዞ ትቀጥላለች ሲሉ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ::

አቶ ኦርዲን በድሪ የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ 2ኛው ተርባይን የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት መጀመሩን አስመልክቶ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል::

ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው ሀገራችን ኢትዮጵያ ፈተናዎችን በብቃት እያለፈች ወደ ብልጽግና የጀመረችውን ጉዞ ትቀጥላለች ብለዋል።

በህዳሴ ግድብ ግንባታ የደረስንበት ውጤት ወደ ምንፈልግበት አስተማማኝ ደረጃ ደርሰን 2ኛው ተርባይን ማመንጨት ጀምሯል" ነው ያሉት።

የኢትዮጵያዊነታችን አርማ የጋራ ጥረታችን አሻራ የሆነው ታላቁ የህዳሴ ግድባችን ሁለተኛ ተርባይን ሀይል ላመነጨበት ለዚህ ታሪካዊ ቀን እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል።

ኢትዮጵያዊያን ፕሮጀክቱ ለስኬት እንዲበቃ በገንዘብ፣ በእውቀት፣ በጉልበትና በሀሳብ አሻራቸውን እያኖሩ መሆኑን ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም