የህዳሴ ግድቡ ሁለተኛ ተርባይን ኃይል ማመንጨት መጀመር ተስፋ የሚሰጥ ታላቅ ብስራት ነው - የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች

88

ነሐሴ 05 ቀን 2014 (ኢዜአ) የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ተርባይን ኃይል ማመንጨት መጀመር ለኢትዮጵያውያን ሁሉ ተስፋ የሚሰጥ ታላቅ ብስራት ነው ሲሉ የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።

ኢዜአ የህዳሴ ግድቡ ሁለተኛ ተርባይን ኃይል ማመነጨት መጀመሩን አስመልክቶ የተለያዩ የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎችን አነጋግሯል።

አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የከተማዋ ነዋሪዎች የግድቡ ስራ ከፍጻሜ እስኪደርስ እያደረጉትን ያለውን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

የግድቡ ሃይል ማመንጨት መጀመር በኢትዮጵያ የተጀመረውን ሰፊ የልማት እንቅስቃሴ እንደሚደግፍ ገልጸው፤ የሀገሪቱን የከፍታ ጉዞ እውን ለማድረግ የራሱን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ተናግረዋል።

መንግስት እና ህዝብ ተቀናጅተው ከሰሩ አገራዊ ብልጽግናን ለማምጣት እንደሚቻል የታየበት ውጤት መሆኑን ገልጸዋል።

በቀጣይ በግብርናው፣ በኢንዱስትሪው፣ በአገልግሎት እና በአምራች ተቋማት የተጀመሩ የብልጽግና ጉዞ ዕውን እንዲሆን መነቃቃት ይፈጥራል ብለዋል።

ለግድቡ ግንባታ መጠናቀቅ ሁለንተናዊ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ያረጋገጡት አስተያየት ሰጪዎቹ፤ ሀገራዊ አንድነትን በመጠበቅ በየተሰማሩበት ሙያ ውጤታማ ለመሆን እንደሚተጉ ተናግረዋል።

ለአፍሪካ ቀንድ እና ለተፋሰሱ ሀገራት የጋራ ዕድገት እና ተጠቃሚነት ግድቡ መሠረት እንደሚሆን ጠቅሰው፤ ግድቡ የሚኖረውን ጠቀሜታ በተመለከተ ለዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ግንዛቤ መፍጠር እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።

በዚህ ረገድ ዲፕሎማቶች፣ ምሁራንና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የቤት ስራ እንዳለባቸው አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም