የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛው ተርባይን ሃይል ማመንጨት ጀመረ

290

ነሃሴ 5/2014/ኢዜአ/ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛው ተርባይን ሃይል ማመንጨት ጀመረ።

የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የመጀመሪያው ተርባይን የካቲት 13 ቀን 2014 ዓ.ም ኃይል ማመንጨት መጀመሩ ይታወሳል።

ግንባታው በብዙ ውጣውረድ ውስጥ በማለፍ በዛሬው እለት ደግሞ ሁለተኛው ተርባይን ሃይም ማመንጨት ጀምሯል።

ግድቡ ካሉት 13 ተርባይኖች መካከል የመጀመሪያው ተርባይን  ከተሳካ ተከላ እና ሙከራ በኋላ የመጀመሪያውን ኃይል ማመንጨት ከጀመረ በኋላ የሁለተኛው ተርባይንም ተሳክቷል።

የመጀመሪያው ተርባይን 375 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳለው መገለጹ የሚታወስ ሲሆን ዛሬ ስራ የጀመረው ተርባይን  ተመሳሳይ ኃይል በማመንጨት በድምሩ 750 ሜጋዋት ኃይል የሚያስገኙ ይሆናል።

የ13ቱም ተርባይኖች ግንባታ ሲጠናቀቅ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ አጠቃላይ የማመንጨት አቅም 5 ሺህ 150 ሜጋ ዋት የሚደርስ ይሆናል።

ግድቡ 145 ሜትር ከፍታና ወደ ጎን ደግሞ 1 ሺህ 780 ሜትር ርዝመት  ያለው ሲሆን በኢትዮጵያውያን የቦንድ ግዥና በመንግሥት በጀት እየተከናወነ መሆኑም ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም