በደቡብ ኦሞ ዞን ወላጆቻቸውን ላጡ ህፃናት ግማሽ ሚሊዮን ብር የሚገመት የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

170

ጂንካ፣ ነሐሴ 03 ቀን ቀን 2014 (ኢዜአ) የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ በደቡብ ኦሞ ዞን ወላጆቻቸውን ላጡ 50 ህፃናት ግማሽ ሚሊዮን ብር የሚገመት የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

ቢሮው የትምህርት መርጃ መሳሪያ፣ የደብተር መያዣ ቦርሣ፣ የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ እና የኮቪድ-19 መከላከያ ግብአቶችን ነው የደገፈው።

“በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ሀሳብ በጂንካ ከተማ ተገኝተው ድጋፉን ያስረከቡት የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ እንዳሻው፤ ሀገራችን አሁን ላይ ያጋጠሟትን ዘርፈ ብዙ ተግዳሮቶች እጅ ለእጅ ተያይዘን ልናሻግራት ይገባል ብለዋል።

ድጋፉ በተወሰነ ደረጃ የተማሪዎቹን ጫና እንደሚያቃልል ገልጸዋል።

በድጋፍ ሥነ ስርዓቱ ወቅት የተገኙት የደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ንጋቱ ዳንሳ ለተደረገው ድጋፍ በህፃናቱ ስም አመስግነዋል።

የቢሮው አመራሮችና ሰራተኞች ከዞኑ ወጣቶችና አመራሮች ጋር በመሆን የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ያካሄዱ ሲሆን በቀጣይም ለአረጋዊያን የቤት እድሳት ያስጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ፤

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም