በጋምቤላ ክልል የተገነቡ የግብርና ልማት ፕሮጀክቶች እየተመረቁ ነው

96

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 3/2014(ኢዜአ) በጋምቤላ ክልል ሁለት ወረዳዎች የተገነቡ የተለያዩ የግብርና ልማት ፕሮጀክቶች እየተመረቁ ነው

የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በተገኙበት እየተመረቁ ካሉት የግብርና ፕሮጀክቶች መካከል ዘመናዊ የአርሶ አደሮች ማሰልጠኛና የሰብል ግብይት  ማዕከላት እንዲሁም  አነስተኛ የመስኖ አውታሮች ይገኙበታል።

ፕሮጀክቶቹ የተገነቡት በአቦቦና ጋምቤላ ወረዳዎች ውስጥ መሆኑ ተመልክቷል።

በየወረዳዎቹ በመንቀሳቀስ እየተካሄደ ባለው የምረቃው ሥነ-ሥርዓት ላይ ሌሎችም  የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና የየአካባቢው ነዋሪዎች መገኘታቸውን የኢዜአ ሪፖርተር ከሥፍራው ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም