በሲዳማ ክልል በአንድ ጀምበር የ25 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ መርሐግብር እየተካሄደ ነው

185

ወንሾ ፣ ሐምሌ 29 ቀን 2014( ኢዜአ) በሲዳማ ክልል በአንድ ጀምበር የ25 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ መርሐግብር በመካሄድ ላይ ነው።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ተወካይ አቶ አሸናፊ ኤልያስ ችግኝ ተከላውን በወንሾ ወረዳ አስጀምረዋል።

በመርሐግብሩ ላይ ወጣቶች፣ሴቶች፣ አርሶ አደሮች የመንግስት ሰራተኞችና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ነው።

በሲዳማ ክልል የ2014 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ሐምሌ 4 ቀን 2014 ዓ.ም መጀመሩ ይታወሳል።

በክልሉ በዘንድሮው መርሐግብር ከ300 ሚሊዮን በላይ ችግኞች ለመትከል መታቀዱ ተገልጿል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ