በአፋር ክልል የክረምት በጎ ፈቃድ መርሐ ግብር ከ200 ሺህ በላይ ወጣቶች ተሳትፎ ያደርጋሉ

109

ሐምሌ 27 ቀን 2014 (ኢዜአ)ከ200 ሺህ በላይ ወጣቶች ተሳትፎ ያደርጉበታል የተባለው የአፋር ክልል የክረምት በጎ ፈቃድ ማስጀመሪያ መርሐግብር ዛሬ ተካሂዷል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ፣ የክልሉ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ አስያ ከማል፣የክልሉ አመራሮች እና የምክር ቤት አባላት ተገኝተዋል።

ለሁለት ወራት በሚቆየው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ200 ሺህ በላይ ወጣቶች እንደሚሳተፉ የአፋር ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስታውቋል።

ወጣቶቹ በአረንጓዴ ልማትና ክብካቤ፣የአካባቢ ጥበቃ፣የአካባቢ ጽዳት፣ደም ልገሳና ተያያዥ የሕብረተሰቡን ችግር የሚፈቱ ስራዎችን እንደሚያከናውኑ ተገልጿል።

በተለይም በጦርነት ከፍተኛ ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች አገልግሎቱን እንደሚሰጡ ተነግሯል።

በበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ 192 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የተለያዩ የልማት ስራዎች ለማከናወን መታቀዱን ቢሮው አመልክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም