የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ የፈተና ውጤት ይፋ ሆነ

2181

ሐምሌ 18 ቀን 2014(ኢዜአ) የ2014 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ መደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ገለፀ፡፡

ቢሮው እንደገለጸው ለፈተና ከተቀመጡ ተማሪዎች መካከል 63.9 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች 50 እና ከዛ በላይ ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል፡፡

ይህም ካለፉት አመታት ከተመዘገቡት ከተማ አቀፍ የ8ኛ ክፍል ውጤቶች አንጻር ሲታይ ከፍተኛ ውጤት ሆኖ መመዝገቡን ነው ቢሮው ያሳታወቀው፡፡

ለውጤቱ መመዝገብም የሁሉም ባለድርሻ አካላት ሚና የላቀ በመሆኑ ቢሮው ይህ ውጤት እንዲመዘገብ ኃላፊነታቸውን ለተወጡ አካላት በሙሉ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

ከዛሬ ሐምሌ 18/2014 ጀምሮ የተማሪዎችን ውጤት ቢሮው በቀጣይ በሚያሳውቀው አድራሻ አማካኝነት ኦንላይን መመልከት እንደሚችሉ ጠቁሟል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ 71 ሺህ 832 ተማሪዎች የስምንተኛ ክፍል ፈተና መውሰዳቸውን ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ተገኘው መረጃ ያሳያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም