የጋምቤላ ክልል መንግስት በክልሉ ተቋማት የሚሰሩ 5 አመራሮችን ከኃላፊነት አነሳ

107

ሐምሌ 16 ቀን 2014 (ኢዜአ) የጋምቤላ ክልል መንግስት በክልሉ ተቋማት የሚሰሩ 5 አመራሮች በብልሹ አሰራር ችግር ምክንያት ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ማድረጉን አስታወቀ።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና የብልጽግና ፓርቲ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ኡሞድ ኡጁሉ እንደገለጹት፤ የክልሉ መንግስት ላለፉት አምስት ቀናት ባደረገው የመንግስትና የፓርቲ ግምገማ አመራሮቹ ከኃላፊነት እንዲነሱ ተደርጓል።

በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ ተቋማት ውስጥ ሲሰሩ የቆዩት አመራሮቹ ከኃላፊነት እንዲነሱ የተደረገው ባለባቸው የብልሹ አሰራር ምክንያት እንደሆነ ገልጸው፤ ፓርቲውና የክልሉ መንግስት የጀመራቸውን አመራር የማጥራት ስራ እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።

በተያያዘ ዜና የጋምቤላ ክልል መንግስት አስቸኳይ ስብሰባውን ዛሬ ከቀትር በኋላ ማካሄድ ጀምሯል።

ካቢኔው የ2014 በጀት ዓመት አፈጻጸም እንዲሁም የ2015 በጀት ዓመት እቅድ ጨምሮ በአስር አጀንዳዎች ላይ ውይይት በማድረግ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ፤

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም