በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በ14 ዓመቱ ታዳጊ ላይ ጉዳት ያደረሱ ተጠርጣሪዎች ተያዙ

75
አሶሳ ግንቦት 10/2010 በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ድባጤ ወረዳ በእረኝነት ላይ በነበረ የ14 ዓመት ታዳጊ ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት አድርሰዋል ያላቸውን ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የዞኑ አስተዳደር ጸጥታ መምሪያ አስታወቀ። የመምሪያው ኃላፊ አቶ ጌታቸው ቤሴ ለኢዜአ እንደገለፁት አመራሮችና የፀጥታ አካላት ከህብረተሰቡ ጋር ባደረጉት ውይይትና ክትትል በታዳጊው ላይ ጉዳት ያደረሱትን አምስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል። በተጠርጣሪዎቹ ላይ አስፈላጊው ምርመራ እየተደረገ መሆኑን የገለጹት የመምሪያው ኃላፊው ባለፈው ሰኞ ጉዳት የደረሰበት ታዳጊ አበጠር ወርቁ  ተጨማሪ ህክምና እንዲያገኝ የአካባቢው ህብረተሰብ የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉንም ተናግረዋል። እንደዚህ ዓይነት ወንጀሎችን ለመከላከል እንዲቻልም የህብረተሰቡን ግንዛቤ ከማሳግ ጀምሮ አስፈላጊው ክትትል እንደሚደረግም አቶ ጌታቸው ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም