በ2014 በጀት ዓመት ወደ ውጭ ከተላኩ የኢንዱስትሪ ምርቶች ከ500 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ

120

ሐምሌ 6/2014(ኢዜአ) በ2014 በጀት ዓመት ወደ ውጭ ከተላኩ የማምረቻ ኢንዱስትሪ ምርቶች ከ500 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ከአምራች ማህበራት ጋር በዘርፉ ያለውን ተግዳሮት ለመፍታት ያለመ ውይይት እያደረገ ይገኛል።

በዚሁ ወቅት የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል እንዳሉት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ወደ ውጭ ከተላኩ የማምረቻ ኢንዱስትሪ ምርቶች ከ500 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል።

ይህም ከ2013 በጀት ዓመት አፈጻጸም ጋር ሲነጻጸር የ100 ሚሊዮን ዶላር ብልጫ እንዳለው ተናግረዋል።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የተለያዩ ማሻሻያዎችን በማድረግ በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ መሰራቱን ጠቅሰዋል።

አብዛኞቹ ችግሮች ከፖሊሲ ማዕቀፍ ጋር የተያያዙ በመሆናቸው ይህን የሚፈታ የፖሊሲ ክለሳ መጠናቀቁንም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም