የሰላም አማራጭ ዐቢይ ኮሚቴ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ወደ ስራ መግባቱን አስታወቀ

500

ሐምሌ 06 ቀን 2014(ኢዜአ) የሰላም አማራጭ ዐቢይ ኮሚቴ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ወደ ስራ መግባቱን አስታውቋል።

የሰላም አማራጭ አብይ ኮሚቴው የመጀመሪያ ስብሰባውን ማካሄዱን የኮሚቴው አባል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገልጸዋል።

አምባሳደር ሬድዋን እንዳሉት ኮሚቴው በአፍሪካ ሕብረት መሪነት ለሚካሄደው ንግግር የራሱን የአሰራርና ሥነምግባር አካሄድ ተወያይቶ ወስኗል።

በንዑሳን ኮሚቴዎች በመደራጀትም ኃላፊነት ተከፋፍሎ ስራውን ጀምሯል ሲሉ አስታውቀዋል።

በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ያለውን ችግር ለመፍታት መንግስት ሰኔ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በሰብሳቢነት የሚመሩት በአጠቃላይ ሰባት አባላት ያሉት የሰላም አማራጭ ዐቢይ ኮሚቴ መሰየሙ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም