1ሺህ 443ኛው የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል በሰላም እንዲከበር በቂ ዝግጅት ተደርጓል- የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን

90

ባህርዳር፤ ሐምሌ 1/2014 (ኢዜአ)፡ በአማራ ክልል ህዝበ ሙስሊሙ የኢድ አል አድሃ አረፋ በአልን ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲያከብር አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጎ ወደ ስራ መገባቱን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የኮሚሽኑ የሚዲያና ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር መሠረት ደባልቄ ለኢዜአ እንደገለጹት የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል  ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከበር አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጎ ወደ ስራ መገባቱን አስታውቀዋል።

የእምነቱ ተከታዮች በአሉን የሚያከብሩባቸው ቦታዎች  ልዩ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ተገቢ የሆነ ስምሪት ተሰጧል ብለዋል።

የአካባቢው ህብረተሰብም በአሉ ያለምንም የጸጥታ ስጋት በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ የቀደመ አንድነቱን ይበልጥ እንዲያጠናክርም ጠይቀዋል።

በተለይ ደግሞ ወጣቱ ከጸጥታ ኃይሉ ጋር በመቀናጀት የአካባቢውን ሰላም ከሰርጎ ገቦች ነቅቶ ሊጠብቅ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ህብረተሰቡ በዓሉ በሚያከበርበት ወቅት አጠራጣሪ ነገሮችን ሲመለከት በአቅራቢያው ለሚገኝ የጸጥታ አካል ፈጥኖ መጠቆም እንዳለበትም አስገንዝበዋል።

ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን በሰላምና በደስታ አክብሮ እንዲውልም የእምነቱ ተከታዮችና የሌሎች እምነት ተከታዮች  የቆየ የመረዳዳትና የመተባበር ባህላቸውን ሊያስቀጥሉ እንደሚገባ አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም