የትምህርት ሚኒስቴር ለተፈናቃይ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

88
አዲስ አበባ መስከረም 3/2011 የትምህርት ሚኒስቴር በኦሮሚያ ምዕራብ ጉጂና በደቡብ አዋሳኝ አካባቢዎች ተፈናቅለው ለነበሩት ዜጎች 96 ሚሊዮን ብር የሚገመት የትምህርት ቁሳቁስና አልባሳት ድጋፍ አደረገ። ትምህርት ሚኒስቴር ድጋፉን ያደረገው በአመቱ የትምህርት መጀመሪያ የትምርቱን ስራ ለማጠናከርና ተገቢ ድጋፍ ለማድረግ  አስቦ ነው ተብሏል። የትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ጥላዬ ጌቴ በተገኙበት  ለሁለቱም ክልል ተወካዮች ርክክብ ተደርጓል። ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፣ በጌዴኦና በምዕራብ ጉጂ ግጭት በተፈጠረበት ወቅት ተማሪዎችም ከወላጆቻቸው ጋር ተፈናቅለው ነበር፣ በወቅቱም ወደ 82 ትምህርት ቤቶች መጠለያ ሆነው ቆይተው ነበር፣ ወደ 36 የሚጠጉ ትምህርት ቤቶች ደግሞ ወድመው ነበር ብለዋል። በመኑም ትምህርት ሚኒስቴር ከዓለም አቀፍ የእርዳታ ሰጪ ድርጅቶችና ከተለያዩ አገሮች ያሰባሰባቸውን ለተጎጂዎች እርዳታ አድርጓል። በሁለቱም ክልሎች ችግሩ ላጋጠማቸው 63 ሺህ 750 ተማሪዎች ሙሉ ዩኒፎርም፣ አራት ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ሳሌዳዎች  ጋር ተደምሮ  ባጠቃላይ 41 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ወጪ መደረጉን  ዶክተር ጥላዬ ገልጸዋል። የትምህርት ቁሳቁሱም ደብተር፣ ቀለም፣ እርሳስና ሌሎችም የትምህረት ግብዓቶች በአጠቃላይ 55 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ድጋፍ በአሜሪካ የዓለም አቀፍ የተራድኦ ትብብር ድርጅት በኩል መደረጉንም ሚኒስተሩ አክለዋል። እንዲሁም ከሁለቱም ዞኖች ለተፈናቀሉ 147 ሺህ ተማሪዎች ለእያንዳንዳቸው፣ ስምንት ደብተር ፣አራት ቀለም፣ ሁለት ማጥፊያ እና ለ50 ተማሪዎች የመረብና የእግር ኳስ ቁሳቁስ እርዳታ መደረጉን ተገልጸዋል። በኦሮሚያ ምዕራብ ጉጂና በደቡብ ጌዲኦ ዞኖች ከተደረገው ድጋፍ ባሻገር ባለው አመት በሱማሌ ክልልና በኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ተፈናቅለው ለነበሩት ዜጎችም ድጋፍ ማድረጉን አስታውሰዋል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም