በሶዶ ከተማ ወጣቶችና ሴቶች ለአረጋውያንና ጎዳና ተዳዳሪዎች ድጋፍ አደረጉ

65
ሶዶ መስከረም 3/2011 በሶዶ ከተማ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችና ሴቶች የዘመን መለወጫ በዓል ምከንያት በማድረግ ለአረጋውያንና ለጎዳና ተዳዳሪዎች የምሳ ግብዥና የአልባሳት ድጋፍ አደረጉ። ድጋፉን አሰባስበው ያበረከቱት በከተማው በበጎ ፈቃድ አገልገሎት የተሰማሩ ስድስት ወጣቶችና የመሃል ክፍለ ከተማ ነዋሪ የሆኑ12 ሴቶች ናቸው፡፡ ከወጣቶቹ መካከል ፍልሞን ማቴዎስ እንደገለፀው በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ የተደረገው የመደመርና በጋራ የማደግ ጥሪ መሰረት ድጋፉን አድርገዋል። ከጓደኞቹ ጋር በመሆን ከህብረተሰቡ ያሰባሰቡትን አልባሳት ለአረጋውያንና ጎዳና ተዳዳሪዎች ማበርከታቸውን አመልክቷል። በሶዶ መሃል ክፍለ ከተማ ነዋሪ ሴቶች በራሳቸው ተነሳኝነት በዓሉን ምክንያት በማድረግ ለአረጋውያንና ጎዳና ተዳዳሪዎች የምሳ ግብዥ ማድረጋቸውን የገለጹት ከሴቶቹ መካከል ወይዘሮ ርብቃ ዲቃሶ ናቸው፡፡ የስልሳ  ዓመት ዕድሜ ያላቸው  አቶ ትግሮ ቲቶ ባለቤታቸው በሞት ሲለይዋቸው አጋዥ በማጣታቸው ጎዳና መውጣታቸውን አመልክተው በተደረገላቸው የምሳ ግብዥና የአልባሳት ድጋፍ መደሰታቸውን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም