ለቤት ኪራይ የወጣው ደንብ እስኪሻሻል ድረስ የኪራይ ዋጋ መጨመር አይቻልም- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

173

ሰኔ 29/2014/ኢዜአ/ ለቤት ኪራይ የወጣው ደንብ እስኪሻሻል ድረስ የኪራይ ዋጋ መጨመር የማይቻል መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ።

ከንቲባዋ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በሰጡት መግለጫ ለቤት ኪራይ የወጣው ደንብ እስኪሻሻል የቤት ኪራይ መጨመር አይቻልም ብለዋል።

ከንቲባዋ በመግለጫቸው የከተማ አስተዳደሩ በየ3 ወሩ የሚታደስ መመሪያ እንደነበረው አስታውሰዋል።

ለቤት ኪራይ የወጣው ደንብ እስኪሻሻል ድረስ የኪራይ ዋጋ መጨመር የማይቻል መሆኑን ገልጸዋል።

በከተማዋ ከፍተኛ የኑሮ ውድነት በመኖሩ በዜጎች ላይ ጫና እያስከተለ በመሆኑ የቤት ኪራይ መጨመር መከልከሉን አስረድተዋል።

በመሆኑም የከተማ አስተዳደሩ በልዩ ሁኔታ አይቶ ደንቡ እስካልተሻሻለ ድረስ ምንም አይነተ የቤት ኪራይ ጭማሪ ማድረግ አይቻልም ብለዋል።

አከራዮችም ሆኑ ተከራዮች ይህንኑ ማወቅ እንዳለባቸው ጠቁመው ክልከላውን ተላልፈው በሚገኙ ላይ ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህ ዙሪያ ዜጎች መብትና ግደታቸውን በቅጡ ተገንዝበው እንዲሰሩም አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም